የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም የ4ጂ አገልግሎት በደቡብ ሪጅን በ12 ከተሞች በይፋ አስጀመረ

By Meseret Awoke

July 06, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮቴሌኮም የአራተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት በደቡብ ሪጅን በ12 ከተሞች በይፋ አስጀምሯል፡፡

የአገልግሎቱ መጀመር ለሀገራዊ እድገትና ብልፅግና ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው ተመልክቷል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚህ ወቅት እንደገለፁት፥ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ ብቻ በ65 ከተሞች ላይ የ4ጂ አገልግሎት ማስጀመር መቻሉን በማንሳት በዚህም ሚሊየኖች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አዲስ የተጀመረው አገልግሎትም ሀዋሳን ጨምሮ ሻሸመኔ፣ ይርጋአለም፣ አለታወንዶ፣ ዲላ፣ አርሲ ነገሌ፣ ቡሌሆራ፣ አዶላ፣ ነገሌ፣ ያቤሎ፣ ሞያሌና ሻኪሶ ከተሞች ላይ ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ ያደርጋል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፡፡

925 ሺህ ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ነው ደሬቴድ የዘገበው፡፡

በአሁን ወቅት ኢትዮ ቴሌኮም 55 ነጥብ 4 ሚሊየን ደንበኞች ያሉት ሲሆን፥ 25ነጥብ 5 ሚሊየኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን።