ስፓርት

በፈረንሳይ በተካሄደ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አስመዘገቡ

By Meseret Demissu

July 06, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በፈረንሳይ በተካሄደ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አበረታች  ውጤቶችን አስመዝግበዋል።

በዚህም በፈረንሳይ፣ ሌንስ በተካሄደ የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር ያሲን ሃጂ  በ13 ደቂቃ ከ18 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ጥላሁን ኃይሌ በ13 ደቂቃ 32 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በሁለተኝነት  አጠናቋል።

በ10 ኪሎ ሜትር ውድድር ወንዶች ደግሞ አንተናየሁ ዳኛቸው በ29 ደቂቃ 04 ሰክንድ በመግባት ውድድሩን በሶስተኝነት ሲያጠናቅቅ በዚሁ   በ10 ኪሎ ሜትር የሴቶች ውድድር ደግሞ አዲሴ ምስለኔው በ31 ደቂቃ ከ 49 ሰክንድ  በመግባት ውድድሯን  በሁለተኛነት አጠናቃለች።

በተጨማሪም በፈረንሳይ ሌንስ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች አቤል ጥላሁን  በ1 ሰዓት 25  ሰከንድ በአራተኛነት ውድድሩን ያጠናቀቀ ሲሆን በሴቶች ደግሞ ጎይተቶም ገ/ስላሴ በ1 ሰዓት 7 ደቂቃ 52 ሰከንድ በበሶስተኛነት ውድድሯን  ማጠናቀቋን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!