የሀገር ውስጥ ዜና

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ከ 300 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ አስጀመረ

By Tibebu Kebede

July 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎችንና የአካባቢውን ኗሪዎች የመጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት የሚፈታ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።

በሾንጋ ወንዝ የሚገነባው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በ300 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነባ ሲሆን÷በ600 ቀናት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ፕሮጀክት በዩኒቨርሲቲው በሁለት ግቢዎች የሚገኙ ተማሪዎችን የመጠጥ ውሃ ችግር መፍታት እንደሚያስችል ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም ፕሮጀክቱ 50 ሺህ ለሚሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ የመጠጥ ፍላጎት የሚያሟላ መሆኑን በዩኒቨርስቲው የሃብትና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተመስገን መኩሪያ ገልፀዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የሾንጋ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታን የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

በተስፋዬ ምሬሳ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!