Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሰሜን ሸዋ ዞንና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በተፈጠረው ችግር ከቀያቸው ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ17 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በተፈጠረው ችግር ከቀያቸው ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ17 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በአጣዬ ከተማ 2ኛ ደረጃ ትምህር ቤት ተጠልለው ከሚገኙ ተፈናቃዮች ጋርም መወያየታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ተፈናቃዮቹ ወደ ዕለት ተዕት መደበኛ እንቅስቃሴያቸው መመለስ እንዲችሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version