ኮሮናቫይረስ

በአውስትራሊያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ዳግም ማገርሸቱ ተሰምቷል

By ዮሐንስ ደርበው

June 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውስትራሊያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት እንደ አዲስ ዳግም ማገርሸቱ ተሰምቷል፡፡

ይህን ተከትሎም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ከግዛት አስተዳዳሪዎች ጋር አስቸኳይ ስብሰባ ማድረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡

በውይይታቸው እንደ አዲስ በመላ ሀገሪቱ ያገረሸውን የኮቪድ-19 ስርጭት መከላከል እና መቆጠጠር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ በዚህም ለቤት ሰራተኞች አስገዳጅ ክትባት እንዲሰጥ እና አዲስ የለይቶ ማቆያ ህጎች ላይ በሚወሰዱ አሰራሮች ዙሪያ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ባለስልጣናቱ ስርጭቱ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን በመግለጽ÷ ሁኔታውን በፍጥነት ለመቆጣጠር ድንበሮችን መዝጋት እና የእንቅስቃሴ ገደብ መጣል እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ