አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በጣሊያን በተደረገ ጄ ሶል ሙንላይት የግማሽ ማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታ ኢትዮጵያውን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል፡፡
በውድድሩ በወንዶች አትሌት ታዬ ግርማ 1 ሰዓት 4 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ አትሌት ዳምጤ ካሹ ታዬ 1 ሰዓት ከ7 ደቂቃ ከ 13 ሰከንድ በመግባት 6ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል፡፡
በሴቶች በተካሄደው ውድድር ደግሞ አትሌት መሰረት እንግዱ አየለ 1 ሰዓት ከ 6 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት ማጠናቀቋ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!