አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የትራንስፖርት እጥርቱን ለማቃለል የ200 አውቶብሶች ግዥ ሊፈጸም መሆኑን የከተማዋ የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አስታውቋል።
የተቋሙ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢቂላ ገላና ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት በረጅም ጊዜ እቅድ የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር ለመቅርፍ 3 ሺህ የሚደርሱ የከተማ አውቶብሶች ለመግዛት ታቅዷል፡፡
በአጭር ጊዜ ውስጥ በተያዘው እቅድ ደግሞ 200 አውቶብሶችን ለመግዛት መወሰኑን ነው ስራ አስኪያጁ የተናገሩት፡፡
በሌላ በኩል የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር በጊዜያዊነት ለማቃላል በቅርቡ የኪራይ አውቶብሶችን ወደ ስራ አስገብቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
በሲሳይ ጌትነት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!