የሀገር ውስጥ ዜና

የኤሌክትሪክ መቆራረጥ የውሃ ስርጭት ላይ ጫና እያሳደረ ነው – የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

By Tibebu Kebede

June 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ሰሞኑን በተፈጠረው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ የውሃ ምርት እና ስርጭት ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ መሆኑን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ የኤሌትሪክ መቆራረጥ ችግሩ በአቃቂ ጉድጓዶች እና ግፊት መስጫ ጣቢያዎች ላይ መፈጠሩን ገልጹ፥ ይህም ውሃ ለደንበኞቹ በወጣው መረሀ ግብር መሰረት እንዳይሰጥ ችግር እንደፈጠረበት አስታውቋል፡፡

በዚህም ገላን አካባቢ፣ ሳሪስ፣ ሀና ማርያም፣ ሀይሌ ጋርመንት፣ ላፍቶ፣ ጀሞ፣ ቆሬ፣ ሳር ቤት፣ ሜክሲኮ፣ ልደታ፣ ጌጃ ሰፈር እና ቤቴል አካባቢዎች ውሃ ለማሰራጨት አልተቻለም ነው ያለው፡፡

ከዚህ ባለፈም በለገዳዲ ጉድጓዶች ላይ በየሰዓቱ የሚከሰተው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በባለስልጣኑ አገልግሎት ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ አንጻርም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የችግሩን ስፋት በመረዳት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠውም ጠይቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!