Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሀገር ውስጥ የተሰራው የማሳያ ታብሌት ለእይታ በቃ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀገር ውስጥ የተሰራው የማሳያ ታብሌት ለእይታ መብቃቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
ሚኒስቴሩ ከ9ኛ እስከ 12 ክፍል ላሉ ተማሪዎች መማሪያና መምህራን ማስተማሪያ የሚሆነው ታብሌት፥ ንድፍ በሀገር ውስጥ እንዲሰራ ትዕዛዝ መስጠቱን ተከትሎ የሙከራ ምርቱ ለእይታ መብቃቱን ገልጿል።
 
ንድፉ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን የተሰራው ታብሌት መንግስት ለመጽሃፍት የሚያወጣውን ወጪ ለማስቀረት እንደሚያግዝና ተማሪዎች ራሳቸውን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አዛምደው እንዲሄዱ ይረዳልም ነው ያለው።
 
ይህን ወደ ተግባር ለማስገባትም ያለውን የኢንተርኔት ግንኙነት ችግር ለመፍታት እንደሚሰራም አስታውቋል።
 
በቀጣይ ሙሉ ለሙሉ ታብሌቱን ሀገር ውስጥ የማምረት እቅድ የተያዘ ሲሆን ለዕይታ የቀረበው ታብሌት ምርት እስከ 70 በመቶ የሀገር ውስጥ እሴትን የሚጠቀም መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Exit mobile version