Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ምርጫው ታሪካዊና ሰላማዊ የሆነ ድባብ ያስተናገደ ነው -የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ታሪካዊና ሰላማዊ የሆነ ድባብን ያስተናገደ ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡

ምሁራኑ ህዝቡን በከፍተኛ ሁኔታ ያሳተፈው ሀገራዊ ምርጫ አንድነትን ይበልጥ ያረጋገጠ አልፎም የህዝቡን መሰልጠንና ጨዋነት በአደባባይ ያሳየ በመሆኑ እጅግ የሚያስደስት ነውም ብለዋል፡፡

አያይዘውም የህዳሴው ግድብ ላይም ይህ አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና እስከ ፍፃሜው ድረስ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም ጠይቀዋል፡፡

በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ላሳዮት ፍፁም ጨዋነት አክብሮታቸውን ገልጸው፥ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የህዝቡን ድምፅ አክብረው በፀጋ ሊቀበሉ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

በታሪክነሽ ሴታ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version