አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትናንትናው የምርጫ ሂደት ትልቅ መልዕክት ያስተላለፈ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የተደረገው ምርጫ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንደሆነ ተናግረዋል።
ድምጻቸውንም ያለ ማንም ጫና ዲሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ እንደሰጡ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
ከምርጫው በፊት ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት እንደነበረባቸው ነገር ግን ከትናንት ጀምሮ ይህ ዜና እስከ ተጠናቀረብት ሰዓት ድረስ ሰላማዊ ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ህብረተሰቡ እና የፖለቲካ ፓርቲዎችን የተሰጠውን የህዝብ ድምጽ ሊያከብሩ ይገባል ነው ያሉት፡፡
በአሁኑ ሰዓት የከተማዋ ነዋሪዎቹ ወደ መደበኛ ስራቸውን ግብተዋል፡፡
በዳግማዊ ደክሲሳ
በዳግማዊ ደክሲሳ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!