የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን በተባበሩት አረብ ኤመሬትስ የስራ ጉብኝት አደረጉ

By Tibebu Kebede

June 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተባበሩት አረብ ኤመሬትስ የስራ ጉብኝት አካሂደዋል።

ለሁለት ቀናት በነበራቸው ቆይታ ከተባበሩት አረብ ኤመሬትስ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

የሁለቱ ሃገራትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንዲሁም በቀጣይ በተለያዩ ዘርፎች ሃገራቱ በሚኖራቸው ትብብር ዙሪያ ተወያይተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በተባበሩት አረብ ኤመሬትስ የነበራቸውን የስራ ተልዕኮ በማጠናቀቅ ወደ ሞስኮ አቅንተዋል፡፡

አቶ ደመቀ ከሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ከማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በሞስኮ በሚኖራቸው የስራ ቆይታ ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለማስረዳት እና በሃገራቱ መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች የበለጠ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!