የሀገር ውስጥ ዜና

በደብረ ብርሃን ከተማ እና በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ይፋ እየሆነ ነው

By Tibebu Kebede

June 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ እና በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ተለጥፎ ዜጎችም ውጤቱን እየተመለከቱት ነው።

በተመሳይ በሰሜን ሸዋ ዞን በተዘዋወርንባቸው የምርጫ ክልሎችና የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት እየተለጠፈ ነው።

የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎች ምርጫው ሰላማዊ ና ዴሞክራሲያዊ እንደነበር ገልፀው ÷ ከዚህ ቀደም ከነበሩ ምርጫዎች የተሻለ ዴሞክራሲ የሰፈነበት እንደነበር ተናግረዋል።

ምርጫ ቦርድ አጠቃላይ ውጤቱን እስኪያሳውቅ ድረስ ሁሉም በትዕግስት መጠባበቅ አለበት ያለት ደግሞ የሰሜን ሸዋ ዞን ምርጫ ቦርድ ማሰተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ አክሊሉ ናቸው።

በአላዩ ገረመው እና በሳምራዊት የሥጋት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!