የሀገር ውስጥ ዜና

በምዕራብ አርሲ ዞን በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የቆጠራ ውጤቶች ይፋ እየሆኑ ነው

By Tibebu Kebede

June 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የቆጠራ ውጤቶች ይፋ እየሆኑ ነው፡፡

የዞኑ የምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ምክትል አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ በቀለ በምርጫ ክልሉ የምርጫ ክልሉ 1 ሚሊየን 101 ሺ 459 መራጮች ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

በዞኑ ድምጽ ለመስጠት 1ሚሊየን 143 ሺህ 116 መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን ÷ እስካሁን ባለው መረጃም ከጠቅላላ የዞኑ መራጮች 96 በመቶ ድምጽ ሰጥተዋል።

የዞኑ የምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ምክትል አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ በዞኑ ባሉ 961 የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

በምስክር ስናፍቅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!