አዲስ አበባ፣ ጥር 15 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ተከታትለው በመግባት አሸናፊ ሆነዋል።
በወንዶች አትሌት ኦሊቃ አዱኛ 2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል።
ኬንያዊው አትሌት ኤሪክ ኪፕሮኖ 2ኛ ደረጃን ሲይዝ ከ3ኛ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል።
በዚህም መሰረት ፀዳት አበጀ 3ኛ፣ ሌንጮ ተስፋዬ 4ኛ፣ ይታያል አጥናፉ 5ኛ፣ ይሁንልኝ አዳነ 6ኛ፣ አይቼው በንቲ 7ኛ፣ ሰይፉ ቱራ 8ኛ፣ ጫሉ ደሶ 9ኛ እንዲሁም ዘውዱ ሀይሉ 10ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።
በሴቶች ምድብ ደግሞ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 9ኛ ደረጃ ተከታትለው በመግባት ውድድሩን በበላይነት ማጠናቀቅ ችለዋል።
በዚህም መሰረት አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ 2 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት ስታጠናቅቅ፤ አትሌት ጉተኒ ሾሜ 2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በመግባት 2ኛ፣ አትሌት በዳቱ ሂርጳ 2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
እንዲሁም አትሌት ትዕግስት ባያቸው፣ አትሌት ደራ ዲዳ፣ አትሌት ሀዊ ፈይሳ፣ አትሌት ብዙነሽ ዳባ፣ አትሌት ኦብሴ አብደታ እና አትሌት ቡዜ ድሪባ ከ4ኛ እስከ 9ኛ ደረጃ ተከታትለው በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል።