አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለምርጫው እስከ ምሽቱ 3፡00 ድረስ አስፈላጊውን ጥበቃ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ ይህን ያለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ድምፅ የሚሰጥበት ጊዜ እስከ ምሽቱ 3፡00 ሰዓት እንዲራዘም መወሰኑን ተከትሎ ነው፡፡
በመዲናዋ ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ችግር እየተካሄደ መሆኑንም ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡
መራጩ ማህበረሰብ ድምፁን በሰላም መስጠጥ እንዲችልም የአዲስ አበባ ፖሊስ በቂ ኃይል መድቦ ጥበቃና ፍተሻውን አጠናክሮ መቀጠሉን አንስቷል፡፡
ስለሆነም ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ ድምፁን ያለስጋት እንዲሰጥ እንዲሁም የፀጥታ አካላትም ተግባራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የምርጫው ሂደት ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ የጎላ ሚና እንደለው እሙን በመሆኑ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!