የሀገር ውስጥ ዜና

በባህርዳር ድምፅ የመሰጠት ሂደቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

June 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህርዳር ከተማ ድምፅ የመሰጠት ሂደቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን የከተማው ምርጫ ክልል ማስተባበሪያ አስታወቀ።

አስተባባሪዋ ወይዘሪት ማህደር አዳሙ በ144 የምርጫ ጣቢያዎች መራጩ ከጠዋት 12 ስዓት ጀምሮ ድምፁን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። በእስከ አሁኑ ሂደትም ምርጫው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ረዣዥም ሰልፎች ይታያሉ ያሉት አስተባባሪዋ በሌሎች የምርጫ ጣቢያዎች አብዛኛውን መራጭ ማስተናገዳቸውን ተናግረዋል።

በአብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቅሬታ ሰሚ አለመቋቋሙ በፓለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታ ፈጥሯል ያሉት አስተባባሪዋ ይህም የተፈጠረው ፈቃደኛ ባለመገኘቱ ነው ብለዋል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!