የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ በቀዳሚዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እየተገነባ ያለውን የዳቦ ፋብሪካ ሂደት ጎበኙ

By Tibebu Kebede

June 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቀዳሚዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እየተገነባ ያለውን የዳቦ ፋብሪካ አጠቃላይ ሂደት ጎበኙ፡፡

የዳቦ ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ ሥራ ሲጀምር በቀን 1 ሚሊየን ዳቦ የማምረት አቅም እንዳለው በማህባረዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በመንግሥት ተነሳሽነት እና በግሉ ዘርፍ ድጋፍ በእያንዳንዱ ዋና ከተማ እስከ 10 የሚደርሱ የዳቦ ፋብሪካዎች እንዲኖሩ የማድረግ እቅድ መኖሩንም አስታውቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!