አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሃዋሳ ከተማ የሂጣታ ዘጠኝ የምርጫ ጣቢያ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ክፍት በማድረግ እየጠጠባበቅን ነው ሲሉ የምርጫ ታዛቢዎችና አስፈጻሚዎች ገለጹ፡፡
በሀዋሳ ከተማ ከምርጫ በፊት የሚደረጉ ዝግጅቶች ተጠናቀው ለመራጩ ህዝብ ዝግጁ ሆነው እየተጠባበቁ መሆናቸውን የምርጫ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች ተናግረዋል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቅኝት ባደረገበት የሂጠታ ዘጠኝ ምርጫ ጣቢያ ዝግጅታቸውን ካጠናቀቁት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፥ የምርጫ ታዛቢዎች ባሉበት ሳጥኑን ባዶ መሆኑን በማረጋገጥ ለምርጫ ዝግጁ መሆናቸውን የተናገሩት የምርጫ ጣቢያው ሀላፊ አቶ አስናቀ ሁንታ ናቸው፡፡
ሃላፊው አብዛኛውን ስራ ማጠናቀቃቸውንም ነው የተናገሩት፡፡
በአሁኑ ሰዓትም የቅድመ ዝግጅት ስራን በማከናወንና በማጠናቀቅ ለመራጮች የምርጫ ጣቢያው ክፍት መደረጉም ነው የተገለጸው፡፡
በብርሃኑ በጋሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!