Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ድምፅ እንዳይሰጥባቸው ተከልክለው የነበሩ 6 የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ እንዲሰጥባቸው ምርጫ ቦርድ ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ድምፅ እንዳይሰጥባቸው በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተከልክለው የነበሩ 6 የምርጫ ጣቢያዎች በነገው እለት ድምፅ እንዲሰጥባቸው የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ወስኗል።
እነዚህ 6 የምርጫ ጠቢያዎች የመራጮች የምዝገባ ሂደት ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጭ አካሂደዋል ተብሎ ነበር ምርጫ እንዳይካሄድባቸው ውሳኔ የተሰጠው።
የምርጫ ተወዳዳሪ ፓርቲዎችና ህብረተሰቡ ባቀረቡት ቅሬታና ጥያቄ መሰረት መራጮች የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብት ስላላቸው ምርጫ ቦርድ ዛሬ በእነዚህ 6 የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ አስተላልፏል።
መራጮች ከዚህ በፊት የተመዘገቡበትን የምርጫ ካርድ ይዘው መጥተው እንደ አዲስ እየተመዘገቡ መምረጥ እንደሚችሉ ምርጫ ቦርድ መግለፁን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version