አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አዳማ ከተማን ጨምሮ በሁሉም የምስራቅ ሸዋ ዞን የምርጫ ጣቢያዎች የቁሳቁስ አቅርቦት መድረሱ ተገለጸ፡፡
ምርጫ ጣቢያዎቹ ንጋት 12 ሰዓት ለመራጮች ክፍት የሚደረጉ ሲሆን የቦታ ርቀት ባለባቸው አካባቢዎች ላሉ አስፈፃሚዎች ማረፊያ ቦታ በጣቢያዎች አካባቢ መዘጋጀቱን የምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ደበሌ ወርቁ ተናግረዋል።
ቀን ላይ የተወሰነ የቁሳቁስ እጥረት የገጠማቸው ስፍራዎች ቢኖሩም በፍጥነት በማምጣት ማሟላት እንደተቻለ አስተባባሪው ገልፀዋል።
በነገው ዕለትም ሁሉም መራጮች ካርድ ባወጡበት ጣቢያ በመገኘት ድምፃቸውን እንዲሰጡ ጠይቀዋል።
በምስራቅ ሸዋ ዞን 1ሺህ 540 የምርጫ ጣቢያዎችና 11 የምርጫ ክልሎች ሲገኙ 5 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ።
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!