አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2013 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ለሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ መሰራጨቱን የዞኑ ምርጫ ቦርድ አስተባባሪ ገልጸዋል፡፡
የዞኑ የምርጫ ቢርድ አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ አክሊሉ እንዳሉት÷ የድምፅ መስጫ ወረቀትን ጨምሮ ሌሎች የምርጫ ግብዓቶች ወደየ ምርጫ ጣቢያዎች ተሰራጭተዋል።
በዞኑ 1 ሺህ 128 የምርጫ ጣቢያወች ዝግጁ ሆነዋል ያሉት አቶ ሙሉጌታ ÷ ከ664 ሺህ በላይ ዜጎች በመራጭነት መመዝገባቸውን አንስተዋል፡፡
የምርጫ ጣቢያዎች ለአካል ጉዳተኞችና አቅመ ደካሞች ምቹ እንዲሆኑ ተደርጓልም ነው ያሉት አስተባባሪው፡፡
ምርጫው ሰላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የመራጩ አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑን የገለጹት አቶ ሙሉጌታ÷ ዜጎች የምርጫ ህግና ደንብ ተከትለው ድምፃቸውን እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል።
በሳምራዊት የስጋት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!