አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ በአጣየና አካባቢው በፀጥታ ችግር ምክንያት የፈረሱ መኖሪያ ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ከ55 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።
የኢንተርፕራይዙ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ጀምበሬ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት፥ የተፈናቀሉ ዜጎችን ክረምት ሳይገባ ቤት እንዲያገኙ ለማስቻል የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማገዝ ታስቦ የተደረገ ድጋፍ ነው።
በደብረሲና ከተማ አካባቢ በባለቤትነት ከሚያስተዳድረው የደን ሃብት ግምታዊ ዋጋው 55 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የሆነ ለቤት መስሪያ የሚውል የባህር ዛፍ እንጨት ድጋፍ ማድረጉን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
በድጋፍ የተበረከተው ፍልጥ እንጨት 13 ሺህ 75 የመኖሪያ ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚያግዝ ነው፡፡
በኢንተርፕራይዙ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘነበ ማንደፍሮ በበኩላቸው ድጋፉ በ30 ሄክታር መሬት ከለማ የባህር ዛፍ ደን ላይ የቀረበ መሆኑን ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!