አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨረሲቲ ከአሜሪካ ሪ ላይፍ ድርጅት ጋር በመተባበር ግምታዊ ዋጋቸው 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመቱ መድሐኒቶችን ለህክምና ተቋማት አበረከተ።
ዩኒቨርሲቲው አርባ አምስት የመድሐኒቶች አይነቶች በአከባቢው ለሚገኙ አስር ሆስፒታሎችና ለአምስት ጤና ጣቢያዎች በልገሳ ሰጥቷል።
መድሐኒቶቹን ለተቋማቱ ያበረከቱት የዩኒቨርስቲው የማህበረሰብ አቀፍ ኢንተርፕራይዝ ምክትል ሃላፊ ዶ/ር ይስሃቅ ዩሱፍ፥ የተደረገው ድጋፍም የህክምና ተቋማቱ በመድሐኒት እጥረት በኩል የሚስተዋሉባቸውን ክፍተቶች ለመሙላት ያግዛል ነው ያሉት።
ድጋፉን ከዩኒቨርስቲው ጋር በመተባበር ያበረከተው በአሜሪካ ክርስቲያን ሪ ላይፍ ድርጅት ሃላፊ ፕሮፌሰር ኦገስት ሲሴ በበኩላቸው ድርጅቱ ላለፋት 11 አመታት መሰል ድጋፎች ሲያበረክት መቆየቱን ገልፀው፣ የዛሬ ድጋፍም የዚሁ አንድ አካል መሆኑን ተናግረዋል።
በምንያህል መለሰ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!