Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቻግኒ ለምርጫ ጣቢያዎች የሚሰራጩ ቁሳቆሶች ርክክብ ተደርገ

 

 አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻግኒ የምርጫ ክልል ውስጥ ላሉ 72 የምርጫ ጣቢያዎች የሚሰራጩ ቁሳቆሶች ርክክብ ተደርጓል::
ለድምጽ መስጫው እለት የሚያገለግሉ ለመራጮች የድምጽ መስጫ ወረቀትን ጨምሮ አስፈጻሚዎች የሚጠቀሟቸው ቅጾች ጭምር መሆናቸውንም የምርጫ ክልሉ ሃላፊ አቶ ዮሃንስ ነጋሽ ነግረውናል።
እነዚህን ቁሳቁሶችም ከዛሬ ጀምሮ ወደየ ምርጫ ጣቢያዎቹ የምናደርስ ይሆናል ያሉት ሃላፊው፥ እስከ ነገ ባለው ቀን ተጠናቀው ለጣቢያዎቹ የሚደርሱ ይሆናል ብለዋል ።
በምርጫ ክልሉ 7 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚወዳደሩ እና ከ49 ሺህ በላይ መራጮች መመዝገባቸውንም አረጋግጠናል።
በይስማው አደራው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version