አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የጀርመኑ ጂ አይ ዜድ የፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱ በአምራች ኢንዱስትሪ ሴክተሮች አካባቢ የስራ እና የኑሮ ከባቢን ማሻሻል እና የስራ እድል ፈጠራን ማሳደግ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል፡፡
ስምምነቱን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ እና የጂ አይ ዜድ በኢትዮጵያ የፕሮጀክት ማናጀር አና ዋልድማን ተፈራርመውታል፡፡
ፕሮጀክቱ በማምረቻው ዘርፍ የስራ እና የኑሮ ከባቢን በማሻሻል እና የሀገር ውስጥ አምራቾችን አቅም በማሳደግ ረገድ አስተዋፅኦ ያደርጋል መባሉን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!