አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህንድና ፓኪስታንን ፍጥጫ ለማርገብ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃገራቸው ከህንድ ጋር ዘወትር የምትወዛገብበትን የካሽሚር ግዛት እልባት ለመስጠት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የማደራደር ሚናውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
ካን በህንድ ከዜግነት አሰጣጥ ጋር በሚነሱ ተቃውሞዎች ዙሪያ ደልሂ በምትሰጠው ምላሽ ላይ ስጋት እንዳላቸውም ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በሀገራቸውና በሕንድ መካከል ሊፈጠር ይችላል ባሉት የጦርነት ስጋት ዙሪያ መወያየታቸውን ገልጸዋል።
በውይይታቸው ወቅትም ትራምፕ ሁለቱን ሃገራት ለማሸማገል ፍቃደኛ እንደሆኑ መግለጻቸውን ጠቅሰዋል።
ካሽሚር ሁለቱ ሃገራት ከሚያነሱት የባለቤትነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የግጭት መንስኤ ሆና ቆይታለች።
ምንጭ ፡- አልጀዚራ