የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች – አቶ ደመቀ

By Tibebu Kebede

January 23, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና አህጉር አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲፈጠር የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።

በስዊዘርላንድ ዳቮስ እየተካሄደ ባለው የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም የአፍሪካ መሪዎች በአንድ መድረክ የተሰባሰቡበት “የአፍሪካ ሰላም ግንባታ” የፊት ለፊት ውይይት ተካሂዷል።