አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር ግምታቸው 2 ሚሊየን ብር የሚሆኑ የኮንስትራከሽን፣የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን፣የተሸከርካሪ ጎማዎችንና ምንጣፍ ግብአቶችን ለመቄዶንያ የአዕምሮና አረጋዊያን መርጃ ማዕከል አበርክቷል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሪት ያስሚን ወሀብረቢየመርጃ ማዕከሉ ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑ አረጋዊያንንና የአዕምሮ ህሙማንን ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውሰው ይህንን አበረታች ተግባር ከመደገፍ አኳያ ማመስገን ብቻ ሳይሆን መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ ከጎናቸው በመሆን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቢኒያም በለጠ ዛሬ የተደረገው ድጋፍ ማዕከሉ በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር እያስገነባ ላለው ባለ ሁለት ቤዝመንት 12 ፎቅ ህንጻ ግንባታ ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው መናገራቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ማዕከሉ በአሁኑ ወቅት በቀን እስከ 20 ሚሊየን ብር ወጪ አለበት ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ ዛሬ የተደረገው እገዛ ያሉባቸውን ችግሮች ከመቅረፍ አኳያ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸው በቀጣይም መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!