አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በሐዋሳ ከተማ በ20 ሚሊየን ብር ሁለገብ የስፖርት ማዕከል ሊገነባ መሆኑን የከተማ መስተዳድሩ አስታወቀ።
የከተማዋ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጥላሁን ካዊሶ÷ የከተማዋን ወጣቶች በስፖርት ሜዳ ውሎ በየጊዜው በውጤት የታጀበ ቢሆንም ከፍተኛ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረት አለ ብለዋል።
በዚህም የተነሳ ለከተማዋ፣ ለክልሉ ሆነ እንደ አገር ከዘርፉ መገኘት ያለበት ጥቅም አልተገኘም ነው ያሉት።
በዚህም የተነሳ ኪሳራው ውስጥ እንደገባን ይሰማናል ያሉት አቶ ጥላሁን÷ በተለይ ስፖርት ፍቅር፣ አንድነት እና ሰላም የሚሰበክበት ትልቁ መሳሪያ ሆኖ ሳለ በዚህ ላይ አበክሮ አለመስራት አግባብ አይደለም ብለዋል።
ከችግሩ የተነሳ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ሊያስጠሩ የሚችሉ ብርቅዬ ወጣቶች አቅም ተደብቋልም ነው ያሉት።
በመሆኑም እነዚህን ነገሮች ከግምት ውስጥ በማስገባት ማዕከሉን መገንባት አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት ስፖርት እና ስፖርተኞች በዓለም ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ መጠን እያንቀሳቀሱ ሲሆን÷ኢትዮጵያ በዚህ የመዝናኛ ኢንዱስትሪ ውስጥ መሪ ተዋናይ አለመሆኗ አሳዛኝ እንደሆነም አስታውቀዋል።
በአገር ደረጃ ለስፖርት የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ ነው ያሉት አቶ ጥላሁን ÷ መሰል የስፖርት ማዕከላትንና ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባት ያላቸው ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ እንድምታ ከፍያለ እንደሆነ ማመልከታቸውንም ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
43,693
People Reached
1,137
Engagements
Boost Post
723
6 Comments
22 Shares
Like
Comment
Share