አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመደበኛ ስብሰባው የ2014 ረቂቅ በጀት ላይ በቀረበለት የበጀት መግለጫ ላይ እየተወያየ ነው።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በፓርላማ ተገኝተው ÷በ2014 ዓ.ም ረቂቅ በጀት ዓመት ውይይት ላይ መንግስት አካታች የፋይናንስ ስርዓትን ለመዘርጋት በርካታ እርምጃዎች መውሰዱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በኢኮኖሚው ዘርፍ ጉልህ የሆኑ ማሻሻያዎች መደረጋቸውንም አንስተዋል።
በዚህም ምግብ ነክ እና ምግም ነክ ባልሆኔ ሸቀጦች ላይ የታክስ ቅነሳ መደረጉን አስታውሰዋል።
-ባለፉት ዓመታት ሲሰራበት የነበረውን የብር ኖቶች በመቀየር በመቻሉም ከባንኮች ውጭ ሲዘዋወር የነበረና በግለሰቦች እጅ የነበረ ገንዘብ ወደ ባንክ እንዲገባ መደረጉ ተገልጿል።
ከዚያም ባለፈ ተንቀሳቃሽ ንብረት ለባንክ ማስያዥያ እንዲውል ተደርጓልም ነው ያሉት።
የኮቪድ – 19 ወረረሽኝ፣ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶች እና የህግ ማስከበር ዘመቻው በኢኮኖሚ ላይ የጎላ ተጽዕኖ እንዳይኖረው መንግስት ከፍተኛ ጥረት ማድረጉንም ገልጸዋል።
-የሸሪያ ህግጋት በሚያከብር መልኩም እንዲበደሩ እና የፋይናንስ ተቋማት ወደ ባንክ እንዲያድጉ የተፈቀደ ሲሆን የፋይናንሻል ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ባንኪንግ ስርዓት ለማጠናከር ተችሏል።
በዚህም ከ 2008 ጀምሮ እየተቀዛቀዘ የመጣውን ኢኮኖሚ በመንግስት የተለያዩ ስራዎች በመሰራታቸው መሻሻል ማሳየቱም ጠቁመዋል።
-በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት የአጠቃላይ የገንዘብ ስርጭት በ17 በመቶ ያደረገ ሲሆን ከተወሰደው አጠቃላይ የብድር መጠንም 64 ነጥብ 5 በመቶው በግሉ ዘርፍ የተወሰደ ነው።
-በኢኮኖሚው ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች ውስጥም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ምንዛሪ ቁጠባ እንዳይሳተፉ የተቀመጠው ክልከላ መነሳቱን ገልጸዋል።
-የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር መንግስት የበጀት ጉድለትን በመሸፈን ከብሄራዊ ባንክ በቀጥታ የሚወሰድን ብድር እንዲቀንስ መደረጉንም አንስተዋል።
ከግብርና ምርቶች ጋር ተያይዞም የተመሰረተውን የውጭ ንግድ ምርቶች መጠን ለማሳደግ ስራዎች ተሰርተዋል እተሰሩም ነው ሲሉ አቶ አህመድ ሺዴ ገልጸዋል።
የተከሰቱ ግጭቶች የተፈጥሮ አደጋዎች ባሉበት ሁኔታ የገቢ አሰባሰቡ አፈፃፀሙ ጠንካራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም የ16 በመቶ እድገት አሳይቷል ፡፡
ሃገሪቱ ያለባትን ከፍተኛ የብድር ስጋት ጫና በሚቀጥሉት ዓመታት ወደ መካከለኛ የብድር ስጋት ለማውረድ የተለያዩ ርምጃዎች እየተወሰዱ ነው፡፡
ከዚህም ውስጥ በመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚወሰደውን የብድርና የኤክስፖርት አፈፃፀሞች በከፍተኛ ሁኔታ ተሻሽሎ ብድር የመክፈል አቅማችን አስተማማኝ ደረጃ እንዲደርስ እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በዚህም ከፍተኛ የዕዳ ጫና ያለባቸውን የእዳ ንብረት አስተዳደር ኮርፖሬሽን በማቋቋም የዕዳ ሽግሽግ እርምጃ ውሳኔ አሳልፏል ብለዋል፡፡
በመሆኑም የህግ ማሻሻያና የህግ ማዕቀፎች በስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!