አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ያዘጋጀው የ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና በሞጆ ከተማ ተጀምሯል ።
በውድድሩ ከአምስት ክልሎችና ከሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ70 በላይ ስፖርተኞች ተሳትፈዋል ።
ዛሬ በመክፈቻው በተካሄደ የሴቶች 10 ኪሎ ሜትር የግል ክሮኖ (የሰዓት ሙከራ) ውድድር ፅጌ አበራ 18 ደቂቃ 39 ሰከንድ ከ62 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ወድድሯን በመጨረስ 1ኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡
በረከት መኮንን 18 ደቂቃ ከ47 ሰከንድ ከ93 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ፣ ቀኖ አለሙ 19 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ ከ21 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ 3ኛ ደረጃን ይዛ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች ።
በወንዶች 13 ኪሎ ሜትር የግል ክሮኖ ውድድር ኪያ ጀማል 17 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ ከ30 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት 1ኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል፡፡
አሚር ጃፋር 17 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ ከ2 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት 2ኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ አግኝቷል ።
ታደሰ ሙሉዬ 18 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ ከ21 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን በማጠናቀቅ የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቱን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!