Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በዞን ደረጃ የተዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በወላይታ ተካሄድ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በዞን ደረጃ የተዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በወላይታ ለወላይታ 6ኛው ዙር “ስፖርት ለሁለንተናዊ ብልፅግና”በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው።
የደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ብሩክ ቡናሮ፥ ከዚህ ቀደም ስፖርት ውድድር ተኮር ብቻ ሆነው መቆየቱን ገልፀው የስፖርት ፍኖተ ካርታ በማርቀቅ ሕብረተሰቡ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ራሱን እንዲከላከል ያግዛል ብለዋል።
የሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ መርክነህ፥ ስፖርትን ባሕል ያደረገ ሕብረተሰብ በመፍጠር ጤናው ተጠብቆ ምርታማ እንዲሆን ትልቅ ፋይዳ አለው ነው ያሉት።
ይህ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የወላይታ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አኩዬ ጌካ ፥ከዚህ በኋላ ታዳጊ አትሌቶችን ለማፍራት ትልቅ ጥረት እንደሚደረግ ቃል ገብተው በውድድሩ የተሳተፉ ሁሉ የሠላምና የለውጥ አሸናፊዎች ናችሁ ብለዋቸዋል።
መርሐ ግብሩ በወላይታ ዞን ስፖርት ምክር ቤት ሲያዘጋጅ ከ21 ሺ በላይ ተሳታፊዎች ተሳትፈዋል
በውድድሩ በሴቶች ድንቅነሽ ኦርሳንጎ ፣ ይፍቱስራ ባልቻና ፅዮን ኃይለሚካኤል በቅደም ተከተል ከአንድ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ወጥተዋል።
በወንዶች ዘርፍ መክሊት መኮንን ፣ ሣሙኤል ባልጣ እና ታደሰ አመኑ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ይዘዋል።
በኢብራሂም ባዲና መለሰ ታደለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version