Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያና ቱርክ በትራንስፖርት ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ቱርክ በትራንስፖርቱ ዘርፍ በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን መግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከቱርኩ የትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር አዲል ካራይስማይሎግሉ ጋር ስምምነቱን መፈራረማቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

በስምምነቱ መሰረት ሃገራቱ በትራንስፖርቱ ዘርፍ ቴክኒካዊ የትብብር ስራዎችን በጋራ ያከናውናሉ ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም የአቅም ግንባታ እና በትራንስፖርት ዘርፍ የልምድ ልውውጥን ያደርጋሉም ነው ያሉት።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version