አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት ለኢትዮጵየ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ በኢትዮጵያ የኮቪድ19 ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የሚውል መሆኑን የድርጅቱ መረጃ ያመላክታል።
የተደረገው ድጋፍም የመተንፈሻ መሳሪያዎች፣ የታካሚዎችን ሁኔታ መከታተያ መሳሪያዎች፣ ደም መለኪያ እንዲሁም ኦክስጂን ማመቂያ መሳሪያዎችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።
ከዚህ ባለፈም የሁለት ቶዮታ ተሽከርካሪዎች ድጋፍም ተደርጓል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!