አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕስ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በወሊሶ ከተማ ትምህርት ቤት እና ሆስፒታል መርቀው ከፍተዋል፡፡
በከተማው የኢፋ ቦሩ አርፋን ወሊሶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የወሊሶ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ የእንስሳት ገበያ ማዕከል፣ የመንገድ ዳር መብራትና የኮብል ስቶን መንገድ ናቸው የተመረቁት፡፡
የኦሮሚያ ክልል የትምህርት ዘርፉን ለማሳደግ እና ለማስፋፋት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ መድቦ ያስገነባቸውን የኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤቶችን እያስመረቀ ይገኛልም ነው ያሉት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፡፡
ተማሪዎች በርትተው በመማር ሀገራቸውን ጠንካራ መሰረት ላይ እንዲያቆሙ አደራ ብለዋል፡፡
በፕሮጀክቶቹ ምርቃት ላይ የፌደራል እና የክልል አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በያዴሳ ጌታቸው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!