የሀገር ውስጥ ዜና

ቦርዱ የድምፅ መስጫ ቀን ስልጠና ቁሳቁስ ስርጭት በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ

By Tibebu Kebede

June 09, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ቀን የስልጠና ቁሳቁስ ስርጭት በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ የምርጫ ስራ የቁሳቁስ ዝግጅት ያለበትን ሁኔታ ለሚዲያ ባለሙያዎች እያስጎበኘ ነው፡፡ የስልጠና ቁሳቁስ ስርጭት በደረሰባቸው አካባቢዎች ቦርዱ ለ150 ሺህ የምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

የድምጽ መስጫ የስልጠና ቁሳቁሶቹ በምርጫ ክልል ወደ ተለዩ አካባቢዎች የሚሰራጩ ሲሆን፥ ከመራጮች ምዝገባ አንጻር የክልል መሪዎች ትብብር እያደገ መምጣቱንም ቦርዱ ገልጿል፡፡

የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጫ እለት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!