Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጀርመን ለኢትዮጵያ ለአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ የሚውል 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ጀርመን ለኢትዮጵያ ለአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ የሚውል 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች፡፡
ሃገሪቱ ድጋፉን ያደረገችው በዓለም የምግብ ፕሮግራም በኩል መሆኑ ታውቋል፡፡
ድጋፉ በትግራይ ክልል በሰላም ማስከበር ዘመቻውና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለተጎዱ ዜጎች የሚውል ነው ተብሏል፡፡
የተደረገው ድጋፍም 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎችን ተደራሽ ያደርጋል መባሉን ከአለም የምግብ ፕሮግራም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ሥደተኞችን ለመደገፍ ይውላል ነው የተባለው፡፡
በአለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ስቴቨን ዌር ኦማሞ ደጋፉ ወቅቱን የጠበቀ መሆን ገልፀው ስለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version