አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖ ልማት ኮሚሽን ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እና ደቡብ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሸን ኢንተር ፕራይዝ ጋር የሁለት የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች የግንባታ ውል ስምምነት ተፈራረመ፡፡
በፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ የውሃ ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንዲሁም የመስኖ ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሮች ኢንጂነር ሳሙኤል ሁሴንና አቶ መኮንን አሰጌ ተገኝተዋል፡፡
ስምምነቱ በሁለቱ ክልሎች የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት መሆኑን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!