Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምስራቅ ሸዋ ዞን ጉምቢቹ ወረዳ የተገነባው ኢፋ ቦሩ ጉምቢቹ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን ጉምቢቹ ወረዳ በ35 ሚሊየን 900 ሺህ ብር የተገነባው ኢፋ ቦሩ ጉምቢቹ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ የኦሮሚያ ክልልብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ተገኝተዋል፡፡
ትምህርት ቤቱ ለሉሜ እና አድአ ወረዳዎች እንዲሁም የምንጃር ሸንኮራ አካባቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደሚችል ተገልጿል፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ወጪየተገነባውና በ5 ወራት ውስጥ የተጠናቀቀው የጉምቢቹ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 18 የመማሪያ ክፍሎች፣ ላብራቶሪ፣ የኮምፒውተር እና መፅሀፍት ቤት ተሟልቶለታል፡፡
በተመሳሳይ በወረዳው በ25 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የውሀ ፕሮጀክት ተመርቋል፡፡
ፕሮጀክቱ ለ5 ሺህ 310 የአካባቢው ነዋሪዎች ለ26 ሺህ ከብቶች ግልጋሎት መስጠት እንደሚችል ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version