Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 10 ወራት ከወርቅ ከ505 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት ውስጥ ከ6 ሺህ 785 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለገበያ በማቅረብ ከ505 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማስገኘት መቻሉን አስታወቀ።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሀብት፣ መስኖ እና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር የ10 ወራት አፈጻጸም ሪፖርትን በአዳማ ከተማ ገምግሟል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት 10 ዓመታት በሃገር አቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከተደረገባቸው መካከል አንዱ በመሆኑ ካለፉት 10 ዓመታት በተሻለ መልኩ ለመለወጥ እና በኢኮኖሚ ማሻሻያ ውስጥ በተቀመጠው መሰረት ስኬታማ ለማድረግ ብቁ እና ተወዳዳሪ የሰው ሀይል የማዘጋጀት ስራ ማከናወኑን አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች አገልግሎት አቋርጠው የነበሩ ፈቃድ ያላቸው የተለያዩ ኩባንያዎች ወደ ስራ ማስገባት አዳዲስ ኩባንያዎች ደግሞ በዘርፉ እንዲሰማሩ ማድረግ ተችሏል ተብሏል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ10 ወራት ውስጥ ከ93 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር እንደቻለም ነው የጠቆመው።

በሌላ በኩል ጥራቱን የጠበቀ ወርቅ ተጣርቶ ወደ ንግድ ባንክ እንዲገባ የማጣሪያ እና የማሻሻያ ስራዎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተሰርቷል መባሉን ኢቢሲ ዘግቧል።

ቋሚ ኮሚቴው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 10 ዓመታት ያስቀመጠውን ዕቅድ ለማሳካት አሁን እያከናወነ ያለው ጅማሮ አበረታች እንደሆነ እና ከዚህ በተሻለ መልኩ እንዲሰራ አሳስቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.