አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፖርቲ የምርጫ ስራዎች አፈፃፀምና ወቅታዊ ጉዳዮች ግምገማ መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተጀምሯል።
በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና የደቡብ ክልል ብልፅግና ፖርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ እንደሚገኝ ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በግምገማ መድረኩ የሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች አስተዳዳሪዎችና የብልፅግና ፖርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊዎች የሚሳተፉ ሲሆን፥ በወቅታዊ የግብርና ስራዎች፣ በምርጫ ስራዎች አፈፃፀምና በወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክሩ ሲሆን ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!