የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን በጋራ ጀመሩ

By Tibebu Kebede

June 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ ሆነው ችግኝ በመትከል የተቋማቱን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አስጀምረዋል።

ተቋማቱ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ናቸው።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል የታቀደውን ስድስት ቢሊየን ችግኝ ለማሳካት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የድርሻቸውን ለመወጣት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በተለይ ሀገር በቀል እና ለምግብነት የሚውሉ እፅዋትን ለመትከል ማቀዳቸውን የኢቢሲ ዘገባ ያመላክታል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!