ዓለምአቀፋዊ ዜና

የእስራኤል ተፎካካሪ ፓርቲዎች አዲስ መንግስት ለመመስረት ተስማሙ

By Tibebu Kebede

June 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የለዘብተኞቹ የሺ አቲድ ፓርቲ መሪ ያይር ላፒድ ስምንት ፓርቲዎችን ያካተተ የጥምር መንግስት ለመመስረት መስማማታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በዙር ለማስተዳደር የተስማሙ ሲሆን የቀኝ ዘመሙ የያሚና ፓርቲው ናፍታሊ ቤኔት ቀዳሚውን የጠቅላይ ሚኒስትር ቦታ ያገኛሉ ተብሏል፡፡

የአሁኑ የፓርቲዎቹ ስምምነት የቤንያሚን ኔታንያሁ የረጅም ጊዜ የስልጣን ዘመን እንዲያከትም ያደርጋል ተብሏል።

ፓርቲዎቹ በሚመሰርቱት መንግስት ይፋዊ የቃለ መሃለ ከመፈጸሙ በፊት ግን የፓርላማው ይሁንታ ያስፈልጋቸዋል ነው የተባለው።

የእስራኤል ፕሬዚዳንት ሬውቨን ሬቭሊንም ፓርላማው የመተማመኛ ድምጽን በተመለከተ ውሳኔ እንዲያሳልፍ እንዲሰበሰብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ህብረቱ 120 መቀመጫዎች ባሉት ክኔሴት (የእስራኤል ፓርላማ) አብላጫ ድጋፍ ካለገኘ በእስራኤል በሁለት ዓመታት ውስጥ ለአምስተኛ ጊዜ ምርጫ የሚካሄድ ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በበኩላቸው የመንግስት ምስረታውን “የክፍለ ዘመኑ ትልቅ ማጭበርበር ነው” ብለውታል፡፡

ምንጭ፦ በቢሲ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!