አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ማሊን በቅርቡ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ከህብረቱ አባልነት ማገዱን አስታወቀ፡፡
ህብረቱ በሃገሪቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለሁለተኛ ጊዜ መፈንቅለ መንግስት መካሄዱን ተከትሎ ነው እገዳውን ያስተላለፈው፡፡
የአፍሪካ ህብረት ባወጣው መግለጫ ሃገሪቱ በአስቸኳይ በሲቪል የሚመራ መንግስት እንድታቋቋም ጠይቋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ስልጣኑን የያዘው ወታደራዊ ሃይል ወታደሮች ወደ ለካምፕ እንዲመለሱም አሳስቧል፡፡
ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ማሊ ላይ ማዕቀብን ጨምሮ ጠንካራ እርምጃዎች ይወሰዳሉም ብሏል፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!