አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ሜልባ የህትመትና ማሸጊያ ተቋም ተመረቀ፡፡
ተቋሙን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ መርቀውታል፡፡
ተቋሙ በአራተኛ ትውልድ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ሲሆን፤ በቀን ከ138 ሺህ በላይ በአመት ደግሞ ከ50 ሚሊየን በላይ መጽሐፍት ማተም ይችላል ነው የተባለው።
ሜልባ ከዚህ ቀደም በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ታትመው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የግልና የትምህርት መፃህፍትን ወጪ ያስቀራል ተብሎ እንደታመነበት ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም አከባቢው ላሉ የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ ጥራት ያለው የህትመት አገልግሎት በመስጠት የውጭ ምንዛሪ ያስገኛል የተባለ ሲሆን፤ ድርጅቱ በህመት ረገድ ያለውን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከማርካቱም በላይ ከ500 ለሚልቁ ዞጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!