Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ድምጻችን ለነጻነታችን” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ አካባቢዎች ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ድምጻችን ለነጻነታችን” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
በሰመራ የተካሄደው ሰልፍ በውስጣዊ የሀገሪቱ ጉዳይ ላይ የውጭ ሃይሎችን ጣልቃ ገብነትና ተፅእኖ የሚያወግዝ ሲሆን በሰልፉ ላይ “በሉአላዊነታችን ላይ ለሚሰነዘሩ ድፍረት አዘል ጫናዎች አንንበረከክም”፣ “ብሔራዊ መግባባት የፈጠረ ግድባችን ለሀገራዊ ብልፅግና መሰረት ነው” ፣ “የኢትዮጵያን ክብር አሳልፎ የሚሰጥ ትውልድ የለም” የሚሉና ሌሎች ተያያዥ መፈክሮች ተሰምተዋል።
እንዲሁም ድምጻችን ለነጻነታችን” በሚል መሪ ቃል በጋምቤላ ከተማ ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን ወጣቶች ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም በላይ የወጣቱን ትብብር የምትፈልግበት ጊዜ ላይ መሆኗን ጠቅሰው የሚፈልግባቸውን ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ሀገሪቱ በርካታ የውጭና የውስጥ ጫና እየተደረገባት እንደሆነ የጠቆሙት ወጣቶቹ ጫናውን መቋቋም የሚቻለው ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድነቱን ሲያጠናክር እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
በተያያዘም ሰልፉ በሀረር ከተማ በተካሄደበት ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በሀገሪቱ በተለይም ባለፉት ሶስት አመታት የውስጥና የውጭ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ና ሀገራችንን ወደ ታላቂነት ሊያሸጋግሩ የሚችሉ ተግባራት ሲከናወኑ ቆተዋል ብለዋል፡፡
በዚህም እኩልንትና ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን የሚያረጋግጥ የጋራ ብልፅግና እውን በማድግ ሀገራችንን ወደ ቀድሞ ሀያልነት እና ገናናነት የመመለስ ብቃት እንዳለን በተግባር ተረጋግጧል ነው ያሉት፡፡
ስልሆነም በዘመናት ቅብብሎሽ የተገነባ ታሪክና ሀገር የተረከበው የዛሬው ታላቅ ትውልድ ከአድርግ አታድርግ የርቀት አዛዦች ነጻ የሚወጣው አንድነቱን አተናክሮ የራሱን እጣ ፋንታ በራሱ ሚወስንበት ኢትዮጵዊ ማንነትና ወኔ በትክክለኛ ጠንካራ መሰረት ላይ ማቆም ሲችል ነው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ድምጻችን ለነጻነታችን” በሚል መሪ ቃል በስልጤ ዞን፣በሆሳዕና እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን በኢትዮጵያ የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወሙ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ወጣቶችና የከተማው ነዋሪዎች ድምጻቸውን ማሰማታቸውን ከየክልሎቹ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version