የሀገር ውስጥ ዜና

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ አፈጻጸም የሚገመግም የውይይት መድረክ ተጀመረ

By Meseret Awoke

May 29, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የስድስት ወራት ስራ አፈጻጸምና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚገመግም የውይይት መድረከ በመቀሌ ከተማ ተጀመረ።

መድረኩ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ሲጀመር የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብረሃም በላይ እንደገለጹት፥ በመድረኩ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ስራዎች ይገመገማሉ።

በተለይም በክልሉ የጸጥታ ሁኔታ፣ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሰብአዊ እርዳታ አሰጣጥ እና የኮሮና ቫይረስ መከላከል ላይ ስለተከናወኑት ተግባራት ውይይት እንደሚደረግባቸው አስታውቀዋል።

እንዲሁም በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስራ አፈጻጸምም እንደሚገመገም ተናግረዋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ በቀጣይ ወራት ትኩረት ሰጥቶ የሚያከናውናቸው ስራዎች አቅጣጫዎች እንደሚቀመጥም ዶክተር አብረሃም ገልጸዋል።

በመድረኩ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የቢሮ ኃላፊዎችና የዞን አመራሮች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!