Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአውሮፓ ህብረት ፋኦ በኢትዮጵያ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል ለሚያደርገው ጥረት 4 ነጥብ 1 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፉ የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) በኢትዮጵያ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል ለሚያደርገው ጥረት 4 ነጥብ 1 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ፡፡

በህብረቱ የተደረገው ድጋፍ በአውሮፓ የህዝብ ጥበቃ እና ሰብአዊ እርዳታ ዘመቻ ክፍል አማካኝነት የተደረገ መሆኑን የፋኦ መረጃ ያመላክታል፡፡

ድጋፉ ፋኦ የበረሃ አንበጣ ለመከላከል የሚያግዙ የኬሚካል መርጫ አውሮፕላን እና ሄሊኮፕተሮችን ለመከራየት ለሚያወጣው ወጪ የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም በመከላከል ዘመቻው ለሚያስፈልጉ መሰረታዊ ግብአት አቅርቦትና ለስራ ማስኬጃ እንደሚውልም ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም የግብርና ሚኒስቴር የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያደርገው ጥረት መሰረታዊ ግብአት አቅርቦት ለማሟላት ይውላልም ነው የተባለው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version