የሀገር ውስጥ ዜና

“ድምፃችን ለነፃነታችን” በሚል በመላ ሀገሪቱ ሰላማዊ ሠልፍ ሊካሄድ ነው

By Tibebu Kebede

May 29, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ድምፃችን ለነፃነታችን” በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ ወጣቶችን ያሳተፈ ሰልፍ ነገ እንደሚካሄድ ተገለፀ።

ሰልፉ የውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና የሚያሳድሩትን ጫና በመቃወም የሚከናወን ነው ተብሏል።

የአሜሪካ መንግስት ከሰሞኑ የጣለው የጉዞ ክልከላና በኢትዮጵያ ላይ የሚያሳድረው ጫና ሀገሪቱ ከድህነት እንዳትላቀቅ ለማድረግ ከመፈለግ የመነጨ በመሆኑ በተለይም ወጣቱ ለሀገር እድገት የበኩሉን በመወጣት የውጭ ጫናን መቃወም ይገባቸዋል ነው የተባለው።

ይህ ወቅት ህዝቡ ይበልጥ አንድነቱን የሚያጠናክርበት እንጂ ህብረ ብሔራዊነቱን የሚያደበዝዝበት ሊሆን እንደማይገባም ተገልጿል።

ከምዕራባውያን ጫና ለመላቀቅ መስራት በትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ማተኮር እንደሚገባም መገለጹን ኢቢሲ ዘግቧል።

መርሐግብሩ ነገ እሑድ ግንቦት 22 ቀን በተመሳሳይ ሰአት በመላ ሀገሪቱ የሚከናወን ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!